ሳምንታዊ የህክምናዊ ውርጃ ደህንነት
ቀደም ባለ የእርግዝና ወቅት ላይ የሚደረጉ ጽንስ ማስወረዶች አነስተኛ የሆነ የሕክምና መወሳሳብ አደጋ አላቸዉ፡፡ የሕክምና መወሳሳብ አደጋ እርግዝናዉ እድገቱ ሲቀጥል አብሮ ይጨምራል፡፡ ለምሳሌ፣ ያልተሟላ ጽንስ ማስወረድ አደጋ ከ 0-10 ሳምንታቶች ለሆኑት እርግዝና 1.6% ነዉ፣ እና 12 ሳምንታቶች ለሆኑት እርግዝና ደግሞ 3.4% ነዉ፡፡ የሕክምና ጽንስ ማስወረድ ከ 13 ሳምንታቶች እና ከዚያ በላይም ደህንነቱ የተጠበቀ ሊሆን ይችላል፣ ነገር ግን የተለዩ ፕሮቶኮሎች ይፈልጋል፡፡
አንቺ ከ 10 ሳምንታቶች በሗላ እና ከ 13 ሳምንታቶች በፊት ጽንስ በምታስወርጂበት ወቅት ምን ልትመለከች ትችያለሽ?
ህክምናዊ ውርጃ ሴቶች እንዲደሙ ያረጋል። ይህ ደም መፍሰስ ከተለመደው የወር ኣበባሽ ሊበዛ ይችላል እና የረጋ ደም ሊኖረው ይችላል። ከ10-11 የእርግዝና ሳምንታት መካከል ያሉ ሴቶች ሊታወቅ የሚችል ነገር ሊያዩ ይችላሉ ወይም ስጋ ሊመስል ይችላል። ይህ የተለመደ ነው እና ሊያስደነግጥሽ ኣይገባም። ውርጃው እንደተጠበቀው የመቀጠሉ ምልክት ነው። እንደ ከባድ የወር ኣበባ ትልልቅ የረጉ ደሞችን ወይም ስጋን ወደ ሽንት ቤት መጣል ነው። ውርጃ ህገ-ወጥ በሆነበት ኣገር የምትኖሪ ከሆነ ሊታወቅ የሚችል ነገርን ሁሉ በጥንቃቄና በሚስጥር ኣስወግጂ።
ደራሲያን:
- በዚህ ድረ ገጽ ላይ የቀረቡት ሁሉም ይዘቶች በብሔራዊ የፅንስ ማስወረድ ፌዴሬሽን፣ Ipas፣ የዓለም ጤና ድርጅት፣ ዲኬቲ ኢንተርናሽናል እና ካራፌም ስር ባሉ ደረጃዎች እና ፕሮቶኮሎች ተገዢ ሆነው በ HowToUseAbortionPill.org ቡድን የተፃፉ ናቸው።
- ብሔራዊ የፅንስ ማስወረድ ፌዴሬሽን (NAF) በሰሜን አሜሪካ ውስጥ የፅንስ ማስወረድ አቅራቢዎች የሙያ ማህበር ሲሆን፣ ምርጫን በሚደግፍ እንቅስቃሴ ላይ ግምባር ቀደም የሆነ ማህበር ነው። በ HowToUseAbortionPill.org ላይ የሚገኘው ይዘት በ NAF ከተለቀቀው የ 2020 ክሊኒካዊ ፖሊሲ መመሪያዎች ጋር አብሮ የሚሄድ ነው።
- Ipas5 ደህንነቱ የተጠበቀ ፅንስ ማስወረድ እና የእርግዝና መከላከያ እንክብካቤ ተደራሽነትን በማስፋፋት ላይ ብቻ ትኩረት አድርጎ የሚሰራ ብቸኛ ዓለም አቀፍ ድርጅት ነው። በ HowToUseAbortionPill.org ላይ የሚገኘው ይዘት በ Ipas ከተለቀቀው የስነ-ተዋልዶ ጤና ክሊኒካዊ ዝመናዎች 2019 ጋር አብሮ የሚሄድ ነው።
- የዓለም ጤና ድርጅት (WHO) ለዓለም አቀፍ የህዝብ ጤና ሃላፊነት ያለበት በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ስር ያለ ልዩ ኤጀንሲ ነው። በ HowToUseAbortionPill.org ላይ የሚገኘው ይዘት በ WHO ከተለቀቀው የ 2012 ደህንነቱ የተጠበቀ ፅንስ ማስወረድ: ለጤና ስርአቶች የቴክኒክ እና የፖሊሲ መመሪያ ጋር አብሮ የሚሄድ ነው።
- ዲኬቲ ኢንተርናሽናል በቤተሰብ ምጣኔ፣ በኤች.አይ.ቪ/ኤድስ መከላከያ እና ደህንነቱ የተጠበቀ ፅንስ ማስወረድ ላይ ከፍተኛ ፍላጎት ባላቸው ትልልቅ ሃገራት ላይ ማህበራዊ ግንዛቤን ማሳደግ ባለው ኃይል ላይ ትኩረት ሰጥቶ ለመስራት በ 1989 የተቋቋመ ለትርፍ ያልሆነ ድርጅት ነው።
- ካራፌም ሰዎች የልጆቻቸውን ቁጥር ለመገደብ እና እንደ ፍላጎታቸው አራርቆ መውለድ እንዲችሉ ለማገዝ ምቹ እና ሙያዊ የሆነ ፅንስ የማስወረድ እንክብካቤ እና የቤተሰብ ምጣኔን አገልግሎቶችን የሚያቀርብ የክሊኒክ ኔትዎርክ ነው።
ዋቢዎች
- “Safe abortion: technical and policy guidance for health systems.” World Health Organization. https://apps.who.int/iris/bitstream/handle/10665/70914/;jsessionid=B7AEEBE4F34809D869F73B1ABA7F6221?sequence=1
- “Clinical updates in reproductive health.” Ipas. https://www.ipas.org/resource/clinical-updates-in-reproductive-health/
- “Clinical policy guidelines for abortion care.” National Abortion Federation (NAF). https://5aa1b2xfmfh2e2mk03kk8rsx-wpengine.netdna-ssl.com/wp-content/uploads/2018_CPGs.pdf