በፍፁም! መጠቀም ያለብሽ ለሁሉም ሰው የሚመከረውን የእንክብል መጠን ብቻ ነው ጥናቶች እንደሚያመላክቱት የሰውነት ክብደት ወይም ከፍተኛ የውፍረት መጠን የመድሀኒቶቹን ስኬታማነት እንደማይቀንሰው ነው፡፡ ስለዚህ ተጨማሪ እንክብሎች ወይም የእንክብል መጠን መውሰድ አይኖርብሽም፡፡
ስለ ውርጃ እንክብሎች በተደጋጋሚ የሚጠየቁ ጥያቄዎች
የውርጃ እንክብሎች አይነትና ጥቅማቸው
እርግዝናሽ መንታ እንደሆነ ብታውቂ እንኳን የእንክብሎቹ የአወሳሰድ መጠን አይቀየርም፡፡ ለመንታ እርግዝና የምትጠቀሚው የአወሳሰድ መጠን ከሌላው ጊዜ የተለየ አይሆንም፡፡ የእንክብል መመሪያዎች ለመንታ እንዲሁም ለነጠላ እርግዝና ተመሳሳይ ናቸዉ፡፡
በጭራሽ! ሁሉም እርግዝና የተለየ ክስተት ነው፡፡ ምን አልባት ከዚ በፊት የውርጃ እንክብል ተጠቅመሽ ከነበረ አሁን በድጋሜ ለሆነው ላልተፈለገ እርግዝና ከመደበኛው ተጨማሪ መጠን ያለው እንክብል መውሰድ አይኖርብሽም፡፡