የኦንላይን ኮርሶች/ትምህርቶች

የሚፈልጉትን የትምህርት አይነት ይምረጡ።

ደህንነቱ በተጠበቀ በህክምና የሚደረግ ውርጃ ስር በልዩ ሁኔታ ለሙያተኛ ባለድርሻ አካላት ታስበው የተዘጋጁ የትምህርትe አይነቶች። ለእርስዎ ተስማሚውን የትምህርት አይነት ይምረጡ።

choose-online-courses

I. የፋርማሲ ሙያተኛ ትምህርት

በህክምና የሚካሄድ ውርጃ (MA) የኦንላይን ትምህርት የተዘጋጀው ለፋርማሲ ሙያተኞች እና የፋርማሲ ሰራተኞች አሰራራቸውን ቅርጽ የሚያስይዙበት እውቀት መስጠትን እና ሙያተኞቹ እርግዝናዎችን ለማቋረጥ በህክምና የሚደረግ ውርጃ እንክብሎችን በመስጠት ረገድ ብቁ እንዲሆኑ ማስቻልን አላማ አድርጎ ነው።

II. የህክምና ተማሪ ትምህርት

በህክምና የሚካሄድ ውርጃ (MA) የኦንላይን ትምህርት የተዘጋጀው ለህክምና ተማሪዎች አሰራራቸውን ቅርጽ የሚያስይዙበት ወሳኝ እውቀት መስጠትን እና በህክምና ውርጃ የሚጠይቁ ወይም ለሚያደርጉ ሴቶች ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ እንዲሆኑ ማስቻልን አላማ አድርጎ ነው።

III. በሰብአዊ እርዳታ መቼቶች በህክምና የሚካሄድ ውርጃ

ይህ የኦንላይን ትምህርት የተዘጋጀው በሰብአዊ እርዳታ መቼቶች በህክምና ስለሚካሄድ ውርጃ (ወይም በመድሀኒት እንክብሎች ስለሚካሄድ ውርጃ) ያለውን እውቀትና ተደራሽነትን ማሳደግን አላማ አድርጎ ነው። በዚህ ትምህርት ስር በሚማሩት መረጃ አማካኝነት በመድሀኒት እንክብሎች የሚካሄዱ ውርጃዎች ደህንነታቸው የተጠበቀ፣ ተደራሽ እና አስተማማኝ እንዲሆኑ መርዳት ይችላሉ። ይህ ትምህርት የተዘጋጀው በድንበር የለሽ የሀኪሞች ቡድን/ Médecins Sans Frontières እና www.HowToUseAbortionPill.org መካከል በሚደረግ ትብብር ነው።

This website may require anonymous cookies and various third party services to function properly. You can read our Terms & Conditions and Privacy Policies. By continuing to use this site you are giving us your consent to do this.