እንዴት ኪኒኖቹን እንደምትጠቀሚበት

ጽንስን ለማስወረድ ሁለት አይነት መድሐኒቶች አሉ፦ ሚፈፕሪስቶን እና ሚሶፕሮስቶል። የኪኒን ጽንስ ማስወረጃ በተሻለ ሁኔታ የሚሰራው ሁለቱም እነዚህ መድሐኒቶች አብረው ከተወሰዱ ነው። ይሁንና፣ ሚፈፕሪስቶን የማይገኝ ከሆነ ሚሶፕሮስቶል ብቻው እርግዝናን ለማቋረጥ ይሰራል፣ እንዲህም ሆኖ ጥንቃቄ ያለው ነው።

በሚፈፕሪስቶን እና ሚሶፕሮስቶል ወይም ደግሞ በሚሶፕሮስቶል ብቻ ጽንስን በጥንቃቄ የምታወርጂባቸው መመሪያዎችን ትፈልጊ እንደሆነ ምረጪ።/

ሚፈፕሪስቶን እና ሚሶፕሮስቶል
ሚሶፕሮስቶል ብቻ
How to Use

ከመጀመርሽ በፊት ኪኒኖቹን መጠቀም ከመጀመርሽ በፊት ላይ ያለው ምክራችንን አንብቢ። የሚከተሉትን አረጋግጪ፦

በሚፈፕሪስቶን እና ሚሶፕሮስቶል ጽንስን የምታስወርጂባቸው መመሪያዎች

በሚፈፕሪስቶን እና ሚሶፕሮስቶል ጽንስን ለማስወረድ ውርጃ አንድ ባለ200 ሚግ ሚፈፕሪስቶን እና ከአራት እስከ ስምንት 200 ማይክሮግራም ሚሶፕሮስቶል መውሰድ ይኖርብሻል። እንዲሁም ህመምን ለማስታገስ እንደ ኢቡፕሮፈን ያለ የህመም ማስታገሻ ኪኒን አጠገብሽ ቢኖር ይሻልሻል። አሰታሚኖፈን እና ፓራሴታሞል በጽንስ ማስወረድ ጊዜ ለሚኖር ህመም አይሰሩም፣ ስለዚህ አይመከሩም።

እርግዝናን ለማቋረጥ ሚፈፕሪስቶን እና ሚሶፕሮስቶል እንዴት አብረው እንደሚወሰዱ እነሆ፦

ደረጃ 1፡

አንድ ባለ200 ሚግ ሚፈፕሪስቶን ኪኒን በውሃ ዋጪ።

ደረጃ 2፡

24-48 ሰዓታት ጠብቂ።

ደረጃ 3፥

4 ሚሶፕሮስቶል ኪኒኖችን (እያንዳንዳቸው 200 ማይክሮግራም) ከምላስሽ ስር አድርጊያቸውና እስኪሟሙ ድረስ ለ30 ደቂቃዎች እዚያው አቆዪያቸው። በእነዚህ 30 ደቂቃዎች ጊዜ ውስጥ መናገር ወይም መብላት የለብሽም፣ ስለዚህ የማትረበሺበት ጸጥ ያለ ቦታ ላይ ብትሆኚ ተመራጭ ነው። ከ30 ደቂቃዎች በኋላ የተወሰነ ውሃ ጠጪና ከኪኒኖቹ የቀረውን ሁሉ ዋጪ። እንዲሁም መሸማቀቅ በቅርቡ የሚጀምር ስለሆነ እንደ ኢቡፕሮፈን ያለ ህመም አስታጋሽ የምትወስጂበት ጥሩ ጊዜ ነው።

4ቱ የሚሶፕሮስቶል ኪኒኖቹን በወሰድሽ በ3 ሰዓታት ውስጥ መድማት እና መሸማቀቅ መጀመር አለበት።

ደረጃ 4 ፥

4ቱ የሚሶፕሮስቶል ኪኒኖቹን ከወሰድሽ ከ24 ሰዓታት በኋላ መድማት ካልጀመርሽ፣ ወይም ደግሞ ጽንስ ማስወረዱ መሳካቱን እርግጠኛ ካልሆንሽ 4 ተጨማሪ የሚሶፕሮስቶል ኪኒኖቹን ከምላስሽ ስር አድርጊያቸው። እስኪሟሙ ድረስ ለ30 ደቂቃዎች እዚያው አቆዪያቸው ከ30 ደቂቃዎች በኋላ የተወሰነ ውሃ ጠጪና ከኪኒኖቹ የቀረውን ሁሉ ዋጪ።

በሚፈፕሪስቶን እና ሚሶፕሮስቶል ጽንስን ለማስወረድ ሌሎች ከግምት ውስጥ መግባት ያለባቸው ነገሮች፦

ሚፈፕሪስቶን እና ሚሶፕሮስቶል ከወሰድሽ በኋላ ምን እንደምትጠብቂ እወቂ። እዚህ

መጥፎ መሸማቀቅ ካጋጠመሽ ኢቡፕሮፈን ህመሙን የሚያስታግስ ጥሩ መድሐኒት ነው። በአብዛኛዎቹ አገሮች ባለ200 ሚግ ጥንካሬ ኢቡፕሮፈን ከመድሐኒት ቤት መግዛት ትችያለሽ (ያለሐኪም ትዕዛዝ)። በየ6-8 ሰዓታት 3-4 ኪኒኖችን (እያንዳንዳቸው 200 ማይክሮግራም) ውሰጂ። ህመምን ለማስታገስ ተጨማሪ ነገር ካስፈለገሽ እንዲሁም በየ6-8 ሰዓታት 2 ታይለኖል (325 ሚግ) ኪኒኖችን መጠቀም ትችያለሽ።

የጽንስ ማስወረድ ሂደቱ ካሳሰበሽ እና ተጨማሪ ድጋፍ የምትፈልጊ ከሆነ www.safe2choose.orgwww.womenhelp.org ወይም www.womenonweb.org ላይ አጋሮቻችንን ማግኘት ትችያለሽ።

የጽንስ ማስወረጃ ኪኒኖቹን ሚፈፕሪስቶን እና ሚሶፕሮስቶል ከተጠቀምሽ ለሕክምና ክትትል የጤና ጣቢያ መጎብኘት የማስፈለግ ዕድሉ አነስተኛ ነው። እነዚህ መድሐኒቶች በጣም ውጤታም ከመሆናቸው የተነሳ የዓለም ጤና ድርጅት የሕክምና ክትትል ያስፈልግሻል ብሎ የሚመክረው የሚከተሉት ከተከሰቱ ብቻ ነው፦

  • ሕመም ከተሰማሽ፣ ወይም ሕመምሽ ከ2 ወይም 3 ቀናት በኋላ መሻል ካልጀመረ። ይህ ከተከሰተ ወዲያውኑ የሕክምና እርዳታን አግኚ።
  • የሕክምና ኪኒኖቹን ከወሰድሽ ከሁለት ሳምንታት በኋላ አሁንም የእርግዝና ምልክቶች የሚሰማሽ ከሆነ።
  • መድማትሽ ከባድ እና ከ2 ሳምንታት በኋላ ካልቀለለ።

በሚሶፕሮስቶል ብቻ ጽንስን የምታስወርጂባቸው መመሪያዎች

ከመጀመርሽ በፊት ኪኒኖቹን መጠቀም ከመጀመርሽ በፊት ላይ ያለው ምክራችንን አንብቢ። የሚከተሉትን አረጋግጪ፦

ሚፈፕሪስቶን በሁኔታሽ ላይ የማይገኝ ከሆነ እርግዝናን ለማቋረጥ ሚሶፕሮስቶልን ብቻ መጠቀም ትችያለሽ።

ሚሶፕሮስቶል ብቻ በመጠቀም ጽንስን ለማስወረድ አስራ ሁለት ባለ200 ማይክሮግራም ሚሶፕሮስቶል ኪኒኖችን መውሰድ ይኖርብሻል። እንዲሁም ህመምን ለማስታገስ እንዲረዳ የህመም ማስታገሻ አጠገብሽ ቢኖር ይሻላል። አሰታሚኖፈን እና ፓራሴታሞል ጽንስ በሚወርድበት ጊዜ ህመምን ለማስታገስ ስለማይሰሩ አይመከሩም።

እርግዝናን ለማቋረጥ ሚሶፕሮስቶል ብቻውን እንዴት እንደምትጠቀሚበት እነሆ፦

ደረጃ 1፥

4 ሚሶፕሮስቶል ኪኒኖችን (እያንዳንዳቸው 200 ማይክሮግራም) ከምላስሽ ስር አድርጊያቸውና እስኪሟሙ ድረስ ለ30 ደቂቃዎች እዚያው አቆዪያቸው። በእነዚህ 30 ደቂቃዎች ጊዜ ውስጥ መናገር ወይም መብላት የለብሽም፣ ስለዚህ የማትረበሺበት ጸጥ ያለ ቦታ ላይ ብትሆኚ ተመራጭ ነው። ከ30 ደቂቃዎች በኋላ የተወሰነ ውሃ ጠጪና ከኪኒኖቹ የቀረውን ሁሉ ዋጪ። እንዲሁም መሸማቀቅ በቅርቡ የሚጀምር ስለሆነ እንደ ኢቡፕሮፈን ያለ ህመም አስታጋሽ የምትወስጂበት ጥሩ ጊዜ ነው።

ደረጃ 2፦

3 ሰዓታትን ጠብቂ።

ደረጃ 3፦

ሌላ 4 የሚሶፕሮስቶል ኪኒኖችን (200 ማይክሮግራም) በምላስሽ ስር አድርጊያቸውና እስኪሟሙ ድረስ ለ30 ደቂቃዎች እዚያው አቆዪያቸው

ደረጃ 4፦

ተጨማሪ 3 ሰዓታትን ጠብቂ።

ደረጃ 5፦

ሌላ 4 የሚሶፕሮስቶል ኪኒኖችን (200 ማይክሮግራም) በምላስሽ ስር አድርጊያቸውና እስኪሟሙ ድረስ ለ30 ደቂቃዎች እዚያው አቆዪያቸው።

ኪኒኖቹን እየወሰድሽ ሳለ መድማት እና መሸማቀቅ መጀመር አለብሽ። ሁሉንም ከመውሰድሽ በፊት መድማት ብትጀምሪም እንኳ ሁሉንም 12 ኪኒኖች መውሰድሽን አረጋግጪ።

በሚሶፕሮስቶል ጽንስን ለማስወረ ሌሎች ከግምት ውስጥ መግባት ያለባቸው ነገሮች፦

ሚሶፕሮስቶልን ከወሰድሽ በኋላ ምን መጠበቅ እንዳለብሽ እወቂ። እዚህ

መጥፎ መሸማቀቅ ካጋጠመሽ ኢቡፕሮፈን ህመሙን የሚያስታግስ ጥሩ መድሐኒት ነው። በአብዛኛዎቹ አገሮች ባለ200 ሚግ ጥንካሬ ኢቡፕሮፈን ከመድሐኒት ቤት መግዛት ትችያለሽ (ያለሐኪም ትዕዛዝ)። በየ6-8 ሰዓታት 3-4 ኪኒኖችን (እያንዳንዳቸው 200 ማይክሮግራም) ውሰጂ። ህመምን ለማስታገስ ተጨማሪ ነገር ካስፈለገሽ እንዲሁም በየ6-8 ሰዓታት 2 ታይለኖል (325 ሚግ) ኪኒኖችን መጠቀም ትችያለሽ።

የጽንስ ማስወረድ ሂደቱ ካሳሰበሽ እና ተጨማሪ ድጋፍ የምትፈልጊ ከሆነ www.safe2choose.orgwww.womenhelp.org ወይም www.womenonweb.org ላይ አጋሮቻችንን ማግኘት ትችያለሽ።

ሚሶፕሮስቶልን ከተጠቀምሽ ለሕክምና ክትትል ጤና ጣቢያ መጎብኘት የማስፈለግ ዕድሉ አነስተኛ ነው። እነዚህ መድሐኒቶች በጣም ውጤታም ከመሆናቸው የተነሳ የዓለም ጤና ድርጅት የሕክምና ክትትል ያስፈልግሻል ብሎ የሚመክረው የሚከተሉት ከተከሰቱ ብቻ ነው፦

  • ሕመም ከተሰማሽ፣ ወይም ሕመምሽ ከ2 ወይም 3 ቀናት በኋላ መሻል ካልጀመረ። ይህ ከተከሰተ ወዲያውኑ የሕክምና እርዳታን አግኚ።
  • የሕክምና ኪኒኖቹን ከወሰድሽ ከሁለት ሳምንታት በኋላ አሁንም የእርግዝና ምልክቶች የሚሰማሽ ከሆነ።
  • መድማትሽ ከባድ እና ከ2 ሳምንታት በኋላ ካልቀለለ።

ደራሲያን:

  • በዚህ ድረ ገጽ ላይ የቀረቡት ሁሉም ይዘቶች በብሔራዊ የፅንስ ማስወረድ ፌዴሬሽን፣ Ipas፣ የዓለም ጤና ድርጅት፣ ዲኬቲ ኢንተርናሽናል እና ካራፌም ስር ባሉ ደረጃዎች እና ፕሮቶኮሎች ተገዢ ሆነው በ HowToUseAbortionPill.org ቡድን የተፃፉ ናቸው።
  • ብሔራዊ የፅንስ ማስወረድ ፌዴሬሽን (NAF) በሰሜን አሜሪካ ውስጥ የፅንስ ማስወረድ አቅራቢዎች የሙያ ማህበር ሲሆን፣ ምርጫን በሚደግፍ እንቅስቃሴ ላይ ግምባር ቀደም የሆነ ማህበር ነው። በ HowToUseAbortionPill.org ላይ የሚገኘው ይዘት በ NAF ከተለቀቀው የ 2020 ክሊኒካዊ ፖሊሲ መመሪያዎች ጋር አብሮ የሚሄድ ነው።
  • Ipas5 ደህንነቱ የተጠበቀ ፅንስ ማስወረድ እና የእርግዝና መከላከያ እንክብካቤ ተደራሽነትን በማስፋፋት ላይ ብቻ ትኩረት አድርጎ የሚሰራ ብቸኛ ዓለም አቀፍ ድርጅት ነው። በ HowToUseAbortionPill.org ላይ የሚገኘው ይዘት በ Ipas ከተለቀቀው የስነ-ተዋልዶ ጤና ክሊኒካዊ ዝመናዎች 2019 ጋር አብሮ የሚሄድ ነው።
  • የዓለም ጤና ድርጅት (WHO) ለዓለም አቀፍ የህዝብ ጤና ሃላፊነት ያለበት በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ስር ያለ ልዩ ኤጀንሲ ነው። በ HowToUseAbortionPill.org ላይ የሚገኘው ይዘት በ WHO ከተለቀቀው የ 2012 ደህንነቱ የተጠበቀ ፅንስ ማስወረድ: ለጤና ስርአቶች የቴክኒክ እና የፖሊሲ መመሪያ ጋር አብሮ የሚሄድ ነው።
  • ዲኬቲ ኢንተርናሽናል በቤተሰብ ምጣኔ፣ በኤች.አይ.ቪ/ኤድስ መከላከያ እና ደህንነቱ የተጠበቀ ፅንስ ማስወረድ ላይ ከፍተኛ ፍላጎት ባላቸው ትልልቅ ሃገራት ላይ ማህበራዊ ግንዛቤን ማሳደግ ባለው ኃይል ላይ ትኩረት ሰጥቶ ለመስራት በ 1989 የተቋቋመ ለትርፍ ያልሆነ ድርጅት ነው።
  • ካራፌም ሰዎች የልጆቻቸውን ቁጥር ለመገደብ እና እንደ ፍላጎታቸው አራርቆ መውለድ እንዲችሉ ለማገዝ ምቹ እና ሙያዊ የሆነ ፅንስ የማስወረድ እንክብካቤ እና የቤተሰብ ምጣኔን አገልግሎቶችን የሚያቀርብ የክሊኒክ ኔትዎርክ ነው።

ዋቢዎች፦

HowToUseAbortionPill.org HowToUseAbortionPill.org መሰረቱን በዩኤስ ካደረገ በ501c(3) ስር ከተመዘገበ ለትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅት ጋር በሽርክና ይሰራል።
HowToUseAbortionPill.org HowToUseAbortionPill.org provides ይዘትን ላይ የተመሰረተ መረጃ ለመረጃነት አላማዎች እንዲያገለግል ብቻ የሚያቀርብ ከመሆኑ በቀር ከህክምና ድርጅት ጋር በሽርክና አይሰራም።

የተጎላበተው በ Women First Digital