ስ ሇ እ ኛ መረ ጃ ከፈሇ ጉ

እኛ ማን ነን

HowToUse በየትኛውም አካባቢ የሚኖሩ ሴቶች ደህንነቱ የተጠበቀ የፅንስ ማስወረድ አማራጭ ተጠቃሚ የመሆን መብት አላቸው ብለው የሚያምኑ እና ይህንን ለማሳካት በቁርጠኝነት የሚሰሩ ግለሰቦች የሚመሩት የመስመር ላይ (online) ማህበረሰብ ነው።

Whoweare_illustration_01

የምንሰራው ስራ

Whowedo_illustration_01

HowToUse የፅንስ ማስወረድ ኪኒኑን በተመለከተ - ኪኒኑ ከመውሰድዎ በፊት ግምት ውስጥ መክተት ስለሚገባዎ ነገር፣ ጥራታቸው የጠበቁ የፅንስ ማስወረድ ኪኒኖች ከየት ማግኘት እንደሚችሉ፣ ደህንነትዎ በማይጎዳ መልኩ እንዴት ሊጠቀሙባቸው እንደሚገባ፣ ምን ውጤት መጠበቅ እንዳለብዎ እና አስፈላጊ ከሆነ መቼ የሕክምና እርዳታ ማግኘት እንዳለብዎ መረጃዎችን እና ማቴርያሎችን የማጋራት ስራ ይሰራል። ሴቶች በራሳቸው መንገድ ፅንስ ማስወረድ የሚችሉበትን እውቀት የማስጨበጥ ስራ ነው የምንሰራው።

የምንሰራበት ቦታ

HowToUse ዓለም አቀፍ ድርጅት ነው- እኛ በመላ አለም ለሚገኙ ሴቶች መረጃ እንሰጣለን። በአሁኑ ጊዜ ድረገፃችን የሚከተሉትን ጨምሮ በ 24 ቋንቋዎች ተተርጉሟል የማ ይ ታ ይ ዎ ት ን ቋ ንቋ ይ ፈ ል ጋ ሉ ? በ ላይ ያግ ኙ ን፡፡ info@howtouseabortionpill.org

Wherewework_illustration_01

ማ ሳሰቢ ያ፡

በ ዚ ህ ድ ረገጽ ላይ ያሉ ገጾች በሙ ሉ ያላቸ ው መ ረ ጃ ት ክ ክ ለ ኛ እንደ ሆ ነ ለማ ረ ጋ ገጥ ሁ ሉ ም ጥ ረት እየተ ደ ረ ገ ነው ፡፡ ነገር ግ ን፣ ሁ ኔታ ዎ ች ከ ጊ ዜ ጊ ዜ የሚ ለወ ጡ ሲ ሆ ን በ ማ ንኛ ው ም ሰአት ላይ የሚ ለ ጠ ፍ ን መ ረጃ በ ተ መ ለ ከ ተ ጸ ፊ ዎ ች ም ንም አይ ነት  ላፊ ነት አይ ወ ስዱ ም ፡፡

Disclaimer_illustration_01

References

Reference_illustration_01
  • Abortion Facts. National Abortion Federation;n.d.
  • Assorted Abortion Resources.Guttmacher; n.d.
  • Clinical Practice Handbook for Safe Abortion. Geneva: World Health Organization; 2014.
  • Creinin, M & Grossman D(2014). Medical Management of First-Trimester Abortion: 143(2):1-18.
  • The Abortion Pill: Medical Abortion with Mifepristone and Misoprostol. The Feminist Women’s Health Center; 2010.
  • Using the combination of Mifepristone and Misoprostol: All you need to know. safe2choose; 2015.
  • Using Misoprostol: All you need to know. safe2choose; 2015.
  • Vekemans, M(n.d.) First trimester abortion guidelines and protocols – Surgical and medical procedures. International Planned Parenthood Federation.
  • Von Hertzen H & Baird D(2006). Frequently asked questions about medical abortion. Contraception: 74(1):3-10.
  • Women's Health Care Physicians. Induced Abortion - ACOG. American College of Obstetricians and Gynecologists,May 2015. Web.

የአገልግሎት ውል

ወደ www.howtousetheabortionpill.org የመግባት እና የመጠቀም (ከዚህ በኋላ “ድረገጽ” እያልን የምንጠራው) እንዲሁም በድረገጹ ባለቤቶች (“እኛ” ወይንም “ራሳችን”) በድረገጹ አማካኝነት የሚቀርቡ መረጃዎች፣ ምስሎች እና ቪድዮዎች የማግኘት እና የመጠቀም መብት ለሚከተሉት ውሎች፣ ደንቦች እና ማስታወቂያዎች (“የአገልግሎት ውሎች”) ተገዢ ይሆናል። በዚሁ ድረገጽ ላይ የሚገኝ መረጃ የሚጠቀም ተጠቃሚ(“እርስዎ” ወይንም “ተጠቃሚው”) ከጊዜ ወደ ጊዜ እኛው ራሳችን ልናሻሽላቸው ለምንችላቸው የአገልግሎት ውሎች ተገዢ እንደሚሆን ተስማምተዋል።

ድረገጹ በግልዎ ከሐኪም የሚያገኙትን የሕክምና ምክር ለመተካት ታስቦ የተዘጋ  ስላልሆነ፣ ሐኪምን በሚተካ መልኩ ሊተማመኑበት አይገባም። የግልዎን የጤና ጥያቄዎች እና አሳሳቢ ሁኔታዎችን በሚመለከት ከሕክምና ባለሙያ ምክር እንዲሹ እንመክራለን።

ድረገጹ ላይ የሚሰፍሩ መረጃዎች ከስህተት የጸዱ መሆናቸው ለማረጋገጥ የሚቻለንን ሁሉ እናደርጋለን። ይሁን እንጂ፣ ይዘቶች ማስታወቂያ ላይ ተመስርተው ከጊዜ ወደ ጊዜ ሊቀያየሩ ይችላሉ፣ ፀሐፊዎቹ ከይዘቱ እውነተኛነት እና ሁሉን አቀፍነት በተያያዘ  ላፊነት አይወስዱም።

ማንኛውም ሰው ይሄንን ድረገጽ ወይንም ድረገጹ ላይ የተለጠፉ ይዘቶች ከመጠቀሙ ወይንም ከሌላ የድረገጹ ተጠቃሚ ጋር በመስመር ላይ ይሁን ከመስመር ውጪ ካደረገው የሐሳብ ልውውጥ ጋር በተያያዘ የግል ጉዳት ወይንም ሞትን ጨምሮ ሊያጋጥመው ለሚችል ማናቸውም ኪሳራ ወይንም ጉዳት እኛ በፍጹም ተጠያቂ አንሆንም።

ፅንስ ማስወረድ በሕግ በሚከለከልባቸው  ገራት የሚኖሩ ዜጎች ድረገፁን ለመጎብኘት ቢወስኑ፣ በድረገጹ መረጃ ሊከሰት ለሚችለው አላግባብ አጠቃቀም ጋር በተያያዘ እኛ ተጠያቂ አንሆንም። በህግ በማይፈቀድበት ቦታ ድረገጹን ለመጠቀም ቢወስኑ፣  ላፊነቱን ራስዎ ይወስዳሉ። የሚኖሩበት ቦታ ሕጎች የማክበር  ላፊነት የራስዎ ነው።

ከድረገጹ አጠቃቀም ጋር በተያያዘ ለሚከሰቱ ማናቸውም ቴክኒካዊ ችግሮች እና ስህተቶች እንዲሁም እነዚህን ችግሮች እና ስህተቶች ተከትለው ሊመጡ ለሚችሉ ማናቸውም ኪሳራዎች እና ጉዳቶች እኛ  ላፊነት አንወስድም። እነዚህ ችግሮች የሚከተሉትን እና ሌሎችን ሊያካትቱ ይችላሉ: የኢሜይል ኮሚዩኒኬሽን፣ ኔትወርክ፣ ሰርቨሮች አለመስራት ወይንም መዘግየት፣ የኢንተርኔት ትራፊክ መጨናነቅ፣ የሶፍትዌር እና  ርድዌር ችግሮች፣ የማናቸውም መሳሪያዎች ስርቆት ወይንም ብልሽቶች።

ድረገጹን ለማበላሸት በፍጹም መሞከር የለብዎትም፣ በተለይም፣ የደህንነት ቁልፍን ለማስወገድ፣ ወይንም ድረገጹን ወይንም ማናቸውም የኮምፒዩተር ስርአት፣ ሰርቨር፣ ራውተር ወይንም ማናቸውም ሌላ ከኢንተርኔት ጋር የተገናኘ መሳሪያ ለማቋረጥ፣ ሰብሮ ለመግባት ወይንም ጉዳት ለማድረስ መሞከር የለብዎትም። ድረገጹ ከማናቸውም ኢንፌክሽኖች፣ ቫይረሶች እና/ወይንም ሌሎች መርዛም ወይንም አውዳሚ ባህሪዎች ካሉዋቸው ኮዶች ነፃ ስለመሆኑ ዋስትና ልንሰጥ አንችልም። የራስዎ የዳታ ግብአት እና ውጤት ደህንነት እና ትክክለኛነት መስፈርቶችን ለማሟላት ተገቢው የአሰራር እና የቫይረስ ፍተሸ የማድረግ  ላፊነት አለብዎ። ወደ ድረገጹ መግባት ካለመቻል ጋር ተያይዘው ለሚቀርቡ ማናቸውም የኪሳራ እና የጉዳት ጥያቄዎች እኛ  ላፊነት ልንወስድ አንችልም።

እኛን፣ እና ሁሉንም ዳይሬክተሮችን፣ አባላቶችን፣ ሰራተኞችን፣ ኮንትራክተሮችን፣ እና በጎፈቃደኞችን (በጥቅሉ “ዋስትና የተሰጣቸው”) ከእርስዎ የድረገጹ አጠቃቀም ወይንም ከአጠቃቀምዎ ጋር በተገናኘ ማለትም እርስዎ ከድረገጹ በወሰዱት መረጃ ምክንያት እነዛ ውሎች እና ደንቦች ከመጣስዎ ጋር እና/ወይንም የሕግ ጥሰት ከመፈጸምዎ ጋር ተያይዞ በእኛ ላይ ሊከሰቱ ከሚችሉ ከማንኛውም እና ከሁሉም ወጪዎች፣ የክፍያ ጥያቄዎች፣ የወጪ ኪሳራ፣ ክፍያዎች፣ የካሳ ጥያቄዎች፣ ክሶች ወይንም ጥያቄዎች፣ ተጠያቂነቶች እና የሕግ፣ የሒሳብ ስራ፣ ወይንም በማንኛውም ክስ፣ የፍርድቤት ሂደት፣ ምርመራ ወይንም በካሳ ጥያቄ ሳቢያ ሌሎች በግልም ይሁን በህብረት ሊያስጠይቁ ከሚችሉ ዋስትና የተሰጣቸው አካላት የሚከስሩዋቸው ወይንም የሙያ ክፍያዎች እንደሚከላከሉልን ማረጋገጫ ሰጥተውናል።

ድረገጹ ወደ ሶስተኛ ወገን ድረገጾች የሚወስዱ አገናኞችን ይዟል። ማናቸውም የውጪ አገናኞች ለእርስዎ ምቾት ሲባል ነው የሚቀርቡት። የውጪ አገናኞችን በራስዎ  ላፊነት ነው የሚጠቀሙት። ማናቸውም ከድረገጹ የሚያገኙዋቸው አገናኞች የማንኛውም ሶስተኛ አካል፣ ከድረገጹ፣ ወይንም ከምርቶቹ እና ከአገልግሎቶቹ ይሁኝታ ያገኙ አይደሉም። ወደ ድረገጹ ወይንም ከድረገጹ ለሚገናኙ ማናቸውም ድረገጾች፣ አገልግሎቶች ወይንም ሌሎች ማቴርያሎች እኛ ላፊነት አንወስድም፣ እንዲሁም እነዚህን ማቴርያሎች ከመጠቀም ተከትለው ሊመጡ ለሚችሉ ማናቸውም ጉዳቶች ተጠያቂ አይደለንም።

ድረገጹ ላይ የሚገኝ መረጃ በማንኛውም ቦታ ጥቅም ላይ እንዲውል የተዘጋ  ስለመሆኑ ዋስትናም ሆነ ውክልና አንሰጥም። እርስዎ ድረገጹን ሲጠቀሙ፣ እንደሱ ለማድረግ እና በድረገጹ የሚገኝ መረጃ ለመጠቀም ሕግ እንደሚፈቅድልዎ ያረጋግጡልናል ማለት ነው።

ከእኛ ጋር ወይንም ከድረገጹ ጋር፣ ወይንም በማንኛውም መንገድ ከድረገጹ አጠቃቀምዎ ጋር በተያያዘ ለሚፈጠር ማንኛውም አለመግባባት የመፍታት ስልጣን ለካናዳ ፍርድቤቶች የተሰጠ መሆኑ በግልጽ ተስማምተዋል፣ በተጨማሪምከእንደዚህ አይነት አለመግባባቶች በተገናኘ በእኛ ላይ ወይንም በድረገፃችን ላይ፣ ወይንም በማናቸው ቅርንጫፎቻችን፣ ተወካዮቻችን፣ ሰራተኞቻችን፣ ኮንትራክተሮቻችን፣  ላፊዎቻችን፣ ዳይሬክተሮቻችን፣ አባላቶቻችን፣ የቴሌኮሚዩኒኬሽን አቅራቢዎች፣ እና የይዘት አቅራቢዎች ላይ ክስ መመስረት ቢፈልጉ ይህንን ማድረግ የሚችሉት በካናዳ ፍርድቤቶች መሆኑም በሚገባ ተስማምተዋል።

ማናቸውም እነዚህ አቅርቦቶች ስልጣን ባለው ፍርድቤት ስህተት ያለባቸው ሆነው ከተገኙ፣ የእነዚህ መጥፎ መሆን የተቀሩት የአገልግሎት ውሎች ተቀባይነት የሚያሳጣ መሆን የለበትም፣ ስለዚህ የተቀሩት አቅርቦቶች የአገልግሎት ውሎች በሙሉ ኃይል እና ተፈፃሚነት ተግባራዊነታቸው ይቀጥላል። የማናቸውም ውሎች መታገድ የውሉ ወይንም የደንቡ ቀጣይ እግድ ሁኔታ ወይንም ማናቸውም ሌሎች ውል ወይንም ደንብ ቀጣይ እግድ የሚያረጋግጥ መሆን የለበትም።

በዚህ ድረገጽ ወይንም በማናቸውም ይዘቱ ወይንም በማናቸውም የእነዚህ የአገልግሎት ውሎች እርካታ ሳይሰማዎ ቢቀር፣ ብቸኛው አማራጭዎ ወደ ድረገፁ መግባት እና ድረገጹን መጠቀም ማቆም ነው።

የግላዊነት ፖሊሲ

www.howtousetheabortionpill.org (ከዚህ በኋላ “ድረገጽ” ተብሎ የሚጠራው) የተጠቃሚዎች ግላዊነት እና ሚስጢራዊነት ለማረጋገጥ በቁርጠኝነት የሚሰራ ድረገጽ ነው። ተጠቃሚዎች ማንኛውም አይነት የግል መረጃቸው ማለትም ስም፣ መኖሪያ አድራሻ፣ ወይንም የኢሜይል አድራሻቸው ሳያጋልጡ ድረገጹን መጠቀም እንዲችሉ በማድረግ ነው ይህንን የምንፈጽመው።

ድረገጹ የድረገጽ ትራፊክ ለመቆጣጠር እና ሌላ አጠቃላይ መረጃ ከድረገጹ ተጠቃሚዎች ለመሰብሰብ የሚያስችለው የኩኪሶች መጠቀምን የሚጨምር የሁሉም የድረገጹ ተጠቃሚዎች ስታትስቲክስ በጥቅሉ ሊሰበስብ ይችላል። በእንደዚህ መልኩ የምንሰበስበው መረጃ ድረገጹን ለማሻሻል እንጠቀምበታለን። ይህ መረጃ ለሶስተኛ ወገኖች ተላልፎ ሲሰጥ የግለሰብ ስም ወይንም ሌላ ማንነት ሊያጋልጥ የሚችል መረጃ ሳያጠቃልል በጥቅሉ ነው።

ተጠቃሚው የድረገጹ ፈጣሪዎችን ማግኘት ቢፈልግ፣ ግለሰቡ ለድረገጹ ያቀረበው መረጃ ከድረገጹ ጥገና ቡድን ወይንም ሌሎች ለእርስዎ ኮሚዩኒኬሽን ምላሽ እንድንሰጥ የሚረዱን አገልግሎት አቅራቢዎች፣ እና በሕግ ከተፈቀደላቸው ውጪ ያለተጠቃሚው ፈቃድ ለማንኛውም ሶስተኛ ወገን ተላልፎ አይሰጥም። ተጠቃሚው የግል መረጃቸው ሊሰጡን ከተስማሙ፣ የሰጡንን መረጃ ለጥያቄ መልስ ለመስጠት ለመሳሰሉ መረጃው ለእኛ ለተሰጠባቸው አላማዎች እናውለዋለን፣ እንዲሁም መረጃውን ተጠቃሚው በመረጠው የአድራሻ ዘዴ እናቀርባለን። ተጠቃሚው ከድረገጹ ጋር በኢሜይል ኮሚዩኒኬት የሚያደርገው ወይንም ድረገጹ ከተጠቃሚው ጋር በኢሜይል ኮሚዩኒኬት የሚያደርገው መረጃ ደህንነት እና ሚስጢራዊነት በሚመለከት ዋስትና ልንሰጥ እንደማንችል እንገልጻለን። በኢንተርኔት የሚደረግ በጥበቃ ስር የማያልፍ የኢሜይል ኮሚዩኒኬሽን ሚስጢሩ የተጠበቀ እንዳልሆነ እና ለጠለፋ፣ ለመጥፋት እና ምናልባትም ለመቀየር የተጋለጠ መሆኑን ተጠቃሚው እውቅና ይሰጣል። በተጠቃሚው እና በድረገጹ በሚደረግ የኢሜይል ኮሚዩኒኬሽን ሳቢያ ለሚፈጠር ማንኛውም ጉዳት እኛ ተጠያቂ አንሆንም።

www.howtousetheabortionpill.org ለሶስተኛ ወገን አገናኝ በሚያቀርብበት ጊዜ፣ እነዛ ድረገጾች ከእኛ የተለየ የራሳቸው የግላዊነት ፖሊሲ ሊኖራቸው ይችላል። ይህ የግላዊነት ፖሊሲ፣ በእነዛ ድረገጾች ላይ አይሰራም እንዲሁም እነዛ ድረገጾች የግላዊነት ፖሊሲ በ www.howtousetheabortionpill.org ላይ አይሰራም። የማንኛውም በዚህ ድረገጽ በኩል የሚያገኙዋቸው ድረገጾች የግላዊነት ፖሊሲ እንዲገመግሙ ጥሪ እናቀርብልዎታለን።

www.howtousetheabortionpill.org ድረገጹን እና የግላዊነት ፖሊሲያችንን በሚመለከት የሚሰጡዋቸው= ሳቦችን በደስታ ይቀበላል። ለማናቸውም ጥያቄዎች ወይንም አስተያየቶች እባከዎ “ያግኙን ቅፃችንን” በመጠቀም ያናግሩን።