ራስን የሚተዳደር ፅንስ ማስወረድ

ይህ የመስመር ላይ ትምህርት ፅንስ ማስወረድ ለማቅረቅ ወይም በቤት ውስጥ ውርጃ እንዲኖር የበለጠ ለመማር ለሚፈልግ ማንኛውም ሰው የተዘጋጀ ነው. በዚህ ኮርስ ውስጥ በሚማሩበት መረጃዎች አማካኝነት ክኒኖች ያሉት ክኒኖች ደህንነታቸው የተጠበቀ, ተደራሽ እና ደህንነቱ የተጠበቀ መሆኑን ማረጋገጥ ይችላሉ. ይህ ኮርስ የሚመረተው በመተባበር ነው መካከል Médecins Sans Frontières እና www.HowToUseAbortionPill.org

ትምህርት 1. እርጉዝ ነኝ?

ስለእርግዝናሽ እርግጠኛ መሆን ትፈልጊያለሽ? ከእርግዝና ማረጋገጫው ጋር በተያያዘ ላለ መረጃ ይህን ቪዲዮ አስሺ

እርግዝና፣ እርጉዝ

እርግዝና – ሁለቱም የታቀዱ እና ያልታቀዱ – በጣም የተለመደ አጋጣሚ ነው።

በዓለም ዙሪያ ከ40% በላይ እርግዝናዎች ያልታቀዱ ናቸው።

ማርገዝ ሳትፈልጊ ቀርተሽ ነገር ግን እርግዘሽ ሊሆን እንደምትችዪ ካሰብሽ ብቻሽን አይደለሽም።

በዚህ ቪዲዩ ላይ እንዴ አንድ እርግዝናን ማረጋገጥ እንደምትችዪ ላይ እናወራለን።

መጀመሪያ እርግዝና የሚከሰተው ወሲብ ከተፈጸመ በኋላ የወንድ ዘር (ነባዘር) ከወንዱ ብልት ወደ የሴቷ ብልት ከተረጨ በኋላ መሆኑን ማወቅ አስፈላጊ ነው።

ወሊድ መከላከያ በወሲብ ጊዜ እርግዝናን ለመከላከል ያግዛል፣ ነገር ግን አሁንም ልታረግዢበት የምትችዪበት ትንሽ ዕድል አለ።

በጊዜው ቀደም ያለ እና በጣም አስተማማኙ የእርግዝና ምልክት የወር አበባ መቅረት ነው።

ወሲብ ፈጽመሽ የወር አበባሽ መዘግየቱን ካስተዋልሽ እርጉዝ ልትሆኚ ትችያለሽ።

ሌሎች የተለመዱ የእርግዝና ምልክቶች ማቅለሽለሽ፣ ራስ ምታት፣ ድካም እና የተለቁና ለስሜት ስስ የሆኑ ጡቶች።

ከወር አበባ መቅረት በተጨማሪም ማናቸውም እነዚህ ምልክቶች ካለሽ እርጉዝ የመሆን ጥሩ ዕድል አለ።

አርግዘሽ ልትሆኚ እንደምትችዪ ካሰብሽ የሽንት እርግዝና ምርመራን በመውሰድ ይህን ማረጋገጥ ትችያለሽ።

የእርግዝና ሙከራዎች በተለምዶ በመድሐኒት ቤቶች እና ሱቆች ውስጥ ይሸጣሉ፣ ወይም ደግሞ አንድ ለማግኘት ወደ ጤና ጣቢያ መሄድ ትችያለሽ።

በኪኒኖች ጽንስ ከማስወረድ በፊት የእርግዝና ምርመራን ማድረግ ግዴታ አይደለም።

የእርግዝና ምልክቶች ኖሮሽ ወይም ደግሞ የእርግዝና ምርመራው አዎንታዊ ሆኖ ነገር ግን እርጉዝ መሆን ካልፈለግሽ እርግዝናውን ለማቋረጥ መወሰን ትችያለሽ።

ጽንስን በኪኒኖች ወይም በቀዶ ጥገና በኩል ማስወረድ ይቻላል።

በዚህ ተከታታይ ቪዲዮ ላይ እውነት የሆነ እና በማስረጃ ላይ የተመሠረተ መረጃን ስናቀርብ እና ከ13 ሳምንታት በፊት በኪኒኖች ጽንስን ማስወረድ ላይ ለሚኖሩ ጥያቄዎች መልስ ስንሰጥ ተከታተዪን።

በሚቀጥለው ቪዲዮዋችን ላይ “እርግዝናዬ ምን ያህል ጊዜ ሆኖታል?” ለሚለው ጥያቄ መልስ እንሰጣለን።

HowToUseAbortionPill.org HowToUseAbortionPill.org መሰረቱን በዩኤስ ካደረገ በ501c(3) ስር ከተመዘገበ ለትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅት ጋር በሽርክና ይሰራል።
HowToUseAbortionPill.org HowToUseAbortionPill.org provides ይዘትን ላይ የተመሰረተ መረጃ ለመረጃነት አላማዎች እንዲያገለግል ብቻ የሚያቀርብ ከመሆኑ በቀር ከህክምና ድርጅት ጋር በሽርክና አይሰራም።

የተጎላበተው በ Women First Digital